❖•ೋ° °ೋ•❖ 💖 ትሁት ልብ 💖 •••••○••••• ❖•ೋ° °ೋ•❖ ╬╬═════════════╬╬ ✍️ፀሃፊ: ናይላ✍️ ╬╬═════════════╬╬ ╭─┅┅┅┅┅─╮ ✯ ክፍል 5 ✯ ╰─┅┅┅┅┅─╯ ሀያት እናቴ ከአንድ ሰዓት በፊት እንድዘጋጅ አድርጋኝ ነበር፣ መምጣታቸውን እየጠበኩ ሳሎን ውስጥ ተቀመጥኩ። አዎ ፈርቼ ነበር ግን ደግሞ ጓጉቼም ነበር። ከቀርፋፋ አንድ ሰዓት በኋላ፣ ከፍተኛ የመኪና ድምፅ ሰማሁ። ልቤ ምትዋን አቋረጠች (ደነገጥኩ) እና እጆቼ ቀዘቀዙ። እነሱ ሊሆኑ ይችላሉ። ከእንጨት የተሰራው ዋናውን በር እናቴ ከፈተችው። አንዲት ሴት ስጦታዎችን ይዛ ከመኪና ስትወጣ አየሁ፣ ሳሎን ውስጥ ሆኜ በመስኮት ነው ያየኋት። ሂክማም ልትቀበላት ወጣች፣ እኔም ሂክማን ተከተልኳት። ሰላም ስላት ትኩር ብላ እኔን መመልከት ጀመረች፣ ይህም እንዳፍር አደረገኝ። "ማሻአላህ፣ ማሻአላህ፣ በጣም ቆንጆ ነሽ ማሻአላህ" አለች ሴትዮዋ። ሰላም ካልኳት በኋላ አቀፈችኝ እኔም መልሼ አቀፍኳት ደግነቷ ፈገግ እንድል አደረገኝ። ሳሎን ውስጥ ተቀመጥን እና ዱዓ አደረገችልኝ። "አሚን" ሂክማ እና እናቴ በአንድ ጊዜ አሉ። እኔም በልቤ አልኩት። "ልጄ ስላረፈደ ይቅርታ አድርጉልኝ፣ ስራ ላይ ነው እና አስቸኳይ ስብሰባ ነበረው። ከእህቱ ጋር በቅርብ ጊዜ ውስጥ ይደርሳል" አለች በደግነት። ሴትዮዋ ብዙ ጥያቄዎችን መጠየቅ ጀመረች፣ አንዳንድ ጥያቄዎችን እንዴት መመለስ እንዳለብኝ አላውቅም ነበር። ስንት ልጆች እንደምፈልግ፣ ምግብ እንደምሰራ ወይም እንደማልሰራ፣ ምን ስራ እንደምሰራ ወዘተ ጠየቀችኝ። በጥበብ በተሞሉት አይኖቿ ውስጥ እንደጓጓች ማየት እችል ነበር። ለግማሽ ሰዓት ያህል ስናወራ እና ጥያቄዎችን ስመልስ ከቆየሁ በኋላ፣ አንድ የመኪና ድምጽ ልቤን በኃይል እንድትመታ አደረጋት። ልጁ እና እህቱ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ለምን እንዲህ እረበሻለሁ። ቅዝቃዜ እና መንቀጥቀጥ ተሰማኝ ይህም እንድደነዝዝ አደረገኝ። እንግዶቹን ለመቀበል ፈልጋ እህቴ በሩ አጠገብ ቆመች። የኮቴ ድምፆች ከፍ እያሉ እና እየከበዱ ሲመጡ እሰማ ነበር። ለእናቴ እና ለእህቴ ሰላምታ የሚሰጡ ሁለት በደንብ የማውቃቸው ድምፆችን ሰማሁ። አሁንም ልመለከታቸው አልቻልኩም፣ ተረብሼ ነበር እናም በትክክል ማሰብ አልቻልኩም። እህቱን ሰላም ለማለት ተነስቼ ቆምኩና ጠበኩ። "አሰላሙ አለይኩም" አለ አንድ የማውቀው የሴት ድምፅ። "ወአለይኩም ሰላም" አልኩና ተመለከትኳት። ፊቴ የቆመችውን ሴት ሳያት አይኖቼን ማመን አቃተኝ፣ ጀሚላ... አቀፍኳትና መሳቅ ጀመረች፣ ሳቋ ልክ እንደ ሚያስቀው ጋዝ ወዲያውኑ እንድስቅ ያደርገኛል። ሁሉም እኛን ይመለከቱን ነበር። ጀሚላ ከእኔ ጋር ተቀመጠች እና በሹክሹክታ ማውራት ጀመርን። ልጁ ከእናቱ ጋር ተቀመጠ፣ አቀማመጡ በጣም የማውቀው ይመስላል ነገር ግን ፊቱን ማየት አልቻልኩም። እናቴን ማናገር ጀመረ። ድምፁ በጣም ጥበብ የተሞላበት እና ቁምነገረኛ ይመስላል። አማማ እና ኮፊያ ለብሶ ስለነበር ፊቱን በትክክል ማየት አልቻልኩም። ልቤ በኃይል መምታቱን እንድታቆም ፊቱን በትንሹም ቢሆን ማየት ብቻ ነው የምፈልገው። ጀሚላ ያደረገችው ነገር ቢኖር እኔን ማየት ከዚያም እሱን ማየት ብቻ ነበር፣ አንዲትም ቃል አልተነፈሰችም። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ እህቴ እና እናቴ ለእንግዶቹ ቡና እና የተወሰነ ጣፋጭ ሰጧቸው። ጀሚላን ስለ ወንድሟ ለመጠየቅ ወሰንኩ። በሹክሹክታ "ጀሚላ ወንድምሽ ነው እንዴ?" ስል ጠየኳት። "አዎ ወንድሜ ነው፣ እና አንቺ ደግሞ በደንብ ታውቂዋለሽ" አለች በቀልድ መልክ። ነገር ግን የጀሚላን ወንድም አግኝቼው እንደማላውቅ መማል እችል ነበር። ከዚያም አክስት ፋጡማ፣ የልጁ እናት በከፍተኛ ድምፅ እንዲህ አለች። "አደም ልጄ፣ ከሀያት ጋር ተነጋግሬያለሁ እሷ ብልህ ሴት ናት እና አፍቃሪ ሰው እንደሆነች መናገር እችላለሁ፣ ላንተ ትክክለኛዋ ሴት ናት።" አደም የሚለውን ስም ስሰማ ወደ እሱ ተመለከትኩ እሱም ወደ እኔ ተመለከተ፣ አለቃዬ አቶ አደም ነበር። ቀጥሎ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አጥቼ በድንጋጤ ደረቅኩ፣ ፊቱ እንደተለመደው ምንም አይነት ስሜት አላሳየም። አይኖቹን እንዳየሁ ወዲያውኑ ፊቴን መለስኩ። የጀሚላ ወንድም አደም ነው። አደም እናቴ የአጎቴ ልጅ ፋሂም የሚስቱ እህት ገና እንዳላገባች የሚገልጽ ዜና እንደሰማች በጣም ተደሰተች እና ወዲያውኑ ለሁሉም ነገረች። ዛሬ ጠዋት ልጅቷን ልናገኛት እንደምንሄድ እና ለእኔ ተስማሚ መሆን አለመሆኗን እንደምናይ ነገረችኝ። ጠዋቱን ሙሉ ያወራችው ለእኔ ምን ያህል እንደጓጓች ብቻ ነበር፣ እኔ በበኩሌ አልጓጓሁም ነበር። በእናቴ ንግግሮች እና ደስታ ምክንያት ወደ ስራ ለመሄድ አርፍጄ ነበር፣ ጀሚላም ዛሬ ከእኔ ጋር ስለምትመጣ እሷም አርፍዳ ነበር። የእናቴን ንግግሮች ስሰማ እና ልጅቷን እንዳገኛት ስታሳምነኝ ለአንድ ሰዓት ከቆየች በኋላ፣ ወደ ስራ እንድሄድ እንድትለቀኝ ስል ብቻ ተስማማሁ። ወደ ስራ ሄድኩ እና ለአንድ ሰዓት ከሰራሁ በኋላ፣ እናቴ ቀድማ እዚያ ስለነበረች በተቻለ ፍጥነት በልጅቷ ቤት መጥቼ እንዳገኛት የሚገልፅ ስልክ ከእናቴ ደረሰኝ። እናቴ ስትደውልልኝ አስፈላጊ ስብሰባ ላይ ነበርኩ፣ አንዲት ልጅን ለማግኘት ስል ብቻ የድርጅቴን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወስን አስፈላጊ ስብሰባ ትቼ መውጣት ነበረብኝ። ከጀሚላ ጋር ወጣሁ፣ እናም እናቴ ወደ ነገረችኝ አድራሻ ሄድን። ጀሚላም ብትሆን ልጅቷ ማን እንደሆነች አታውቅም ነበር። ወደ ቤቱ ስገባ አየኋት፣ እይታዋን ዝቅ አድርጋ እጆቿን ትመለከት ነበር። የተሻለው ነገር እሱ እንደሆነ ስለማውቅ እኔም እይታዬን ዝቅ አደረኩ። ጀሚላ ሰላም እንዳለቻት መሳቅ ጀመረች ከዚያም እሷም ሳቀች፣ የማውቀው ሳቅ ነበር። የልጅቷ እናት ብዙ ጥያቄዎችን ጠየቀችኝ፣ በጣም ጥሩ ሰው ነበሩ ማለት እችላለሁ። ከጥቂት ዝምታ በኋላ እናቴ ሀያት የሚለውን ስም ስትጠራ ትንሽ ገረመኝ። እናቴ እንድመጣና እንዳያት የለመነችኝ ይህች ልጅ ማን እንደሆነች ማየት ነበረብኝ። እራሷ ሀያት ነበረች፣ በድርጅቴ ውስጥ የምትሰራው ያቺው ሀያት። የተረበሸ ፊቷን ማየት እችል ነበር። ሀያት? የኔ ሰራተኛ... ይህ እጣ ፈንታ በእኔ ላይ እየተጫወተ ያለው ጨካኝ ቀልድ መሆን አለበት። ሀያትን በዚያ መንገድ አስቤያት አላውቅም፣ እንዴትስ እንደዛ ላስብ እችላለሁ? እሷ ሰራተኛዬ ናት እኔ ደግሞ አለቃዋ ነኝ፣ በመካከላችን ያለው ነገር ያ ብቻ ነው። እይታዬን መለስኩ እና ለእናቴ ምን እንደምናገር ማሰብ ጀመርኩ። ያለ በቂ ማብራሪያ ሀያትን ለማግባት ፈቃደኛ እንዳልሆንኩ ብገልፅ፣ በጣም እንደምታዝን አውቃለሁ እናቴ ስታዝን ማየት ደግሞ አልችልም። ደግሞስ በጋብቻው ብስማማስ? ከዚያ ምን ይፈጠራል? ሀያት እኔ የማገባት አይነት ሴት አይደለችም፣ በጣም ጫጫታ ታበዛለች እና የራሷን ሀሳብ አጥብቃ የምትይዝ ናት፣ በምወስናቸው ውሳኔዎች ላይ እና ስራ አስኪያጅ እንደመሆኔ መጠን በማደርገው በእያንዳንዱ ነገር ላይ ሁልጊዜ በተዘዋዋሪ መንገድ አስተያየት ትሰጣለች። ሳቋ ደግሞ ያ አላህ በጣም የሚያናድድ እና የሚያበሳጭ ነው፣ ደግሞም መቼም ቢሆን በስርዓት የምትሰራ ልጅ አይደለችም። እናቴ እንዴት እችሂ ልጅ ለእኔ ትመጥናለች ብላ ልታስብ ቻለች? **** 👉 ክፍል 6 ከ 150 ሪያክሽን በኋላ ይቀጥላል…...
https://t.me/halalislamicstory/1021